- Contact Us
- Help by E-MAIL
- COPYRIGHT ©2008-2014CVASC,ALL RIGHTS RESERVED
የመስመር( ኦን ላይን ) ላይ ቅድመ ግምገማ ማመልከቻ ሂደት መመሪያ
በመጀመሪያ ማመልከቻዎን በመስመር ወይም በ (ኦን ላይን )ላይ ያስገቡ
የማመልከቻ ሂደቶች
1ኛ ደረጃ .ማመልከቻዎን በመስመር ላይ ያስገቡ
ይህ ዌብሳይት(ይህ ድህረ ገጽ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የቻይና ቪዛ ለሚያመለክቱ አመልካቾች ነው።እባክዎን ትክክለኛውን ቦታ መምረጥዎን ከምስሉ ላይ ያረጋግጡ (በገጹ ላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ምልክት ያድርጉ)
1. የግል መለያ ይፍጠሩ እና ይግቡ (በገጹ የላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ምልክት ያድርጉ
2. ሁሉም አመልካቾች (የሆንግ ኮንግ እና የማካዎ ቪዛ አመልካቾችን ሳይጨምር) የማመልከቻ ቅጹን በመስመር ላይ መሙላት አለባቸው
2.1. የቪዛ ማመልከቻ ቅጹን በመስመር ላይ ይሙሉ
2.2. የፓስፖርት ፎቶ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ሁሉንም የደጋፊ ሰነዶችን ይጫኑ።
2.3. አስገባ የሚለውን ቁልፍ ጫን ያድርጉ
አስፈላጊ
· በማረጋገጫ ገጹ ላይ የማስረከቢያ ቁልፍን እንደገና ጫን ማድረግ አለብዎት አለበለዚያ ሁኔታዎ በመጠባበቅ ላይ ይቆያል፡፡ መጫንዎን ያረጋግጡ
· የኦንላይን ክፍያ እስካሁን አልተጀመረም፤ ማመልከቻዎት የመስመር (ኦንላይን )ላይ ግምገማውን ካለፈ በኋላ ወደ ቪዛ ማእከል ሲሄዱ ይክፈሉ፡፡
3. የመስመር ላይ ግምገማን ይጠብቁ. ሁኔታው በግምገማ ላይ ይሆናል
1. ተጨማሪ ሰነዶችን ወይም ማሻሻያዎችን የሚጠይቅ ኢሜይል ሊደርስዎት ይችላል። በዚህ ጊዜ ሁኔታዎ ተቀባይነት አላገኘም ወይም ውድቅ ሆንዋል በሚልዎት ጊዜ አሻሽለው መላክ ይገባዎታል
2. ማመልከቻዎ ግምገማውን ማለፉን የሚያረጋግጥ ኢሜይል ሊደርስዎት ይችላል የእርስዎ ሁኔታ ከዚያም የመስመር ላይ( ኦንላይን) ግምገማ መጠናቀቁን ሲገልጽልዎ እባክዎን የኢሜል አባሪ ቪዛ ማመልከቻ የመጀመሪያ ገጽ እና የመጨረሻ ፊርማ ያለበትን ገጽ ከሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ጋር ይዘው ወደ ቪዛ ማእከል (ደረጃ 2 ይመልከቱ)
3. በማንኛውም ጊዜ ሁኔታውን ለማየት ወደ መለያዎ (ድህረ ገጽ )መግባት ይችላሉ።
ዶክመንት ለማስገባትና ክፍያ ለመክፈል ምንም አይነት ቀጠሮ መያዝ አያስፈልጎዎትም
የማመልከቻ ሂደት
2ኛ ደረጃ ከኦንላይን ግምገማ በኋላ በቪዛ ማእከል ዶክመንተዎን ያቅርቡ (ምንም ቀጠሮ አያስፈልግም)
1. ወደ ቪዛ ማእከል ይሂዱ እና የሚከተሉትን ሰነዶች ያስገቡ (አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ)፡፡
1.1 የቪዛ ማመልከቻ ፎርም እና (ከግምገማ ማረጋገጫ በኋላ የተላከ የኢሜል አባሪ)
1.2 የመጀመሪያው የቪዛ የማመልከቻ ፎርም ገጽ 1 እና የመጨረሻው ፊርማ ያለበትን ገጽ 7
1.3 ዋናውን ፓስፖርት እና አሮጌ ፓስፖርት
1.4 አንድ በቅርቡ የተነሱት ጉርድ ፓስፖርት ሳይዝ ከለር ፎቶ
1.5 ለ s1 እና Q1 ቪዛ አመልካቾች የጋበዣችሁን ወይም የዘመድ የወዳጅነት ማረጋገጫማቅረብ ይኖርባቸዋል::
2. የቪዛ ክፍያ ይክፈሉ
u ማመልከቻውን በሚያስገቡበት ጊዜ ክፍያዎን በቪዛ ማእከል ውስጥ በጥሬ ገንዘብ ይክፈሉ፡፡
3ኛደረጃ ሰነዶችዎን ይሰብስቡ
ማመልከቻዎን በቪዛ ማእከሉ ካስገቡበት ቀን ጀምሮ
§ ለመደበኛ አገልግሎት አራት(4)የሥራ ቀን ሰነዶዎችን(ፓስፖርተዎትን) መረከብ ይችላሉ፡፡
§ ለፈጣን አገልግሎት ሶስት (3 )የስራ ቀን ሰነዶዎችን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
Ø ሰነዶችዎን ለመውሰድ ሲመጡ ማመልከቻዎን ለማስገባት በመጡ ግዜ የተቀበሉትን ደረሰኝ ማቅረብ አለበዎት
u የአመልካቶች ማመልከቻ ማስገቢያ ሰአት ከ ጥዋቱ 3፡00 እስከ 9፡00
u የዶክመንት መረከቢያ ሰዓት ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00